በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው ወላይታ ዲቻ ከሊቢያው አል ኢቲሃድ የሚገናኝ ይሆናል።
በሊቢያ ፕሪሚየር ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አል አሀሊ ቤንጋዚን የገጠመው አል ኢትሀድ ጨዋታውን 3ለ0 በማሸነፉ የኮንፌዴሬሽን ቦታን አግኝቷል። ውጤቱን ተከትሎ አል ኢትሀድ በኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ወላይታ ድቻን የሚገጥም ይሆናል።
ወላይታ ዲቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ከሲዳማ ቡና ተገናኝቶ መሸነፊ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ሲዳማ ቡና በጨዋታው ላይ ማሰለፍ የማይገባውን ተጫዋች አሰልፏል በሚል ውጤቱ እንዲሰረዝ፤ ውጤቱ ለወላይታ ዲቻ በፎርፌ እንዲሰጥና የዋንጫውም አሸናፊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።
ሲዳማ ቡና ለአለምአቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ያስገባው ይግባኝ እንዲቋረጥ መወሰኑም አይዘነጋም። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












