የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ፤ ቦሩሲያ ዶርትሞንድ እና ስቱትጋርት ተጫዋች በአውሮፓውያኑ 2008 ኪሳራ እንዳጋጠመው ከገለጸ ወዲህ የፈተና ህይወት ሲያሳልፍ መቆየቱን ዘ ሰን ዘግቧል።
ኢሚል በ107 ክሶች ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፤ በቀረበበት በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ተብሎ የ2 አመት እስር ተፈርዶበታል። የቀድሞው ተጫዋች የቀረበበት ክስ በሙሉ ከውዝፍ ዕዳ እና ታክስ በአግባቡ ካለመክፈል ጋር የተያያዘ መሆኑም ተመላክቷል።
ጀርመናዊው የ63 አመቱ ኢሚል ቅጣቱ የተወሰነበት በሃገሩ ፍርድ ቤት እንደሆነም ታውቋል። የቀድሞው ግብ ጠባቂ ከአውሮፓውያኑ ከ1995-97 ለማንችስተር ሲቲ የተጫወተ ሲሆን፤ ከዚያ ቀደም ብሎ ለቦሩሲያ ዶርትሞንድ እና ስቱትጋርት በድምር 550 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።
በ1980 ምስራቅ ጀርመን የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ ስትሆን አስደናቂ ብቃቱን ሲያሳይ፤ በ1982 እና በ1986 አለም ዋንጫም አገሩን መወከል ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












