የምዕራብ ለንደኑ ክለብ የማንችስተር ዩናይትዱን የክንፍ መስመር ተጫዋች የግሉ ለማድረግ መቃረቡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በዩናይትድ እንደማይፈለግ የተነገረው አሌሃንድሮ ጋርናቾ ሰማያዊዎቹን ለመቀላቀል በግል ጥቅማ ጥቅም ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሱ ታውቋል። ቀሪ ጉዳይ የሚሆነው በኈቱ ክለቦች መካከል የዝውውር ሂሳቡን በተመለከተ ውይይት ማድረግ ሲሆን፤ የአርጀንቲናዊው ተጫዋች የስታንፎርድ ብሪጅ ጉዞ የማይቀር ነው ተብሏል።
የቤንጃሚን ሼሽኮ ዝውውር ያጠናቀቀው ዩናይትድ ሌሎች ተጫዋቾችን ለማምጣት ከቡድን ስብስቡ የማይፈልጋቸውን በቶሎ የመሸጥ ፍላጎት አለው።
ቼልሲ ምንም እንኳን ጋርናቾ በሚሰለፍበት የግራ መስመር የክንፍ ቦታ የአርቢ ላይብዚሹን ዣቪ ሲሞንስን ለማስፈረም ቢቃረብም የቡድን ስብስቡን ለማስፋት ዝውውሩን መፈጸሙ አይቀርም እየተባለ ይገኛል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












