እንግሊዛዊው ታዳጊ ከአርሰናል ሃል ኢንድ አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን በማደግ በተለይም ባሳለፍነው የውድድር አመት አስደናቂ ብቃቱን ማሳየት ችሏል።
ተጫዋቹ ኢታን የውሉ የመጨረሻ አመት ላይ ይገኝ የነበረ ሲሆን፣ በርካታ ክለቦች ፍላጎት ማሳየታቸው ለአርሰናል ስጋት ፈጥሮ ቆይቷል። ኢታን ንዋኔሪ በመድፈኞቹ ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን አዲስ የአምስት አመት ኮንትራት ሲፈርም፣ጠቀም ያለ ሳምንታዊ ደመወዝ እንደተሰጠውም ታውቋል።
ተጫዋቹ ውሉን ከፈረመ በኋላ በሰጠው አስተያየት ሁለገብ ተጫዋች በመሆኑ አሰልጣኙ በሚሰጠው ሃላፊነት ለቡድኑ ውጤት የሚቻለውን እንደሚያደርግ ተናግሯል። ንዋኔሪ ባሳለፍነው የውድድር አመት ይጠቀምበት የነበረውን 53 ቁጥር በመለወጥ 22 ቁጥር ወስዷል።
በአዲሱ የውድድር አመት ከአርሰናል ቁልፍ ተጫዋቾች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












