አስቶን ቪላ በፊት መስመር ላይ ያለበትን ክፍተት ለመሸፈን ኢቫን ጉሳንድን ከኒስ አምጥቷል።
ቪላ ለ24 አመቱ አጥቂ 35 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ያደረገ ሲሆን፤ የረጅም ጊዜ ውል አስፈርሞታል። የአሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ቡድን ተጫዋቹን ጆን ዱራን ከለቀቀበት የጥር ወር የዝውውር መስኮት አንድቶ ሲፈልገው እንደነበርም ተነስቷል።
በቡድን ስብስቡ ውስጥ የእንግሊዛዊው አጥቂ ኦሊ ዋትኪንስም ቆይታ እስካሁን ባለመታወቁ ተጫዋቹን ለማስፈረም እንዳስገደዳቸው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። ፈረንሳዊው አጥቂ ጉሳንድ ባሳለፍነው የውድድር አመት ለኒስ ባደረጋቸው 42 ጨዋታዎች 13 ግብ ሲያስቆጥር፣ 10 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል።
አስቶን ቪላ የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በቀጣይ ሳምንት አርብ ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












