ወሳኙን የአማካኝ መስመር ተጫዋቹን ጄምስ ማዲሰንን በጉዳት ያጣው ቶተንሃም ተተኪ የሚሆኑ ተጫዋቾችን በማፈላለግ ላይ ይገኛል።
ማዲሰን ያጋጠመው የACL ጉዳት አዲሱን የውድድር አመት በሙሉ ከሜዳ ሊያርቀው ይችላል የተባለ ሲሆን፤ ክለቡ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት በስፍራው ላይ ተጫዋች ማምጣቱ የማይቀር ነው ተብሏል።
ቶተንሃም አሁን ላይ በጥብቅ እየፈለገው የሚገኘው ተጫዋች በጣሊያን ሴሪ ኤ ለኮሞ የሚጫወተውን ኒኮ ፓዝን ሆኗል። ኒኮ ፓዝ ባሳለፍነው የውድድር አመት 35 ጨዋታዎችን ለኮሞ በማድረግ 6 ግብ ሲያስቆጥር፤ 8 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን ለቡድን ጓደኞቹ አቀብሏል።
የ20 አመቱ ስፔናው በሪያል ማድሪድ ማሰልጠኛ ያደገ እና በሁለቱ ክልቦች መካከል በተደረሰ ስምምነት መሰረት፤ የሚሸጥ ከሆነ ሎስ ብላንኮዎቹን የትርፍ ተካፋይ ያደርጋቸዋል።
ቶተንሃም በቀጣይ ቀናት ለተጫዋቹ ዝውውር ይፋዊ ጥያቄ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












