የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚሽኑ ወደ መቀሌ በማቅናት ከሐምሌ 22 እስከ 24 ከጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከሲቪክ ማህበረሰብ፣ ከህወሓት አመራሮች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውጤታማ ውይይቶች ማድረጉን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ በሰጡት ማብራሪያ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለማስጀመር የሚረዱ ውይይቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መደረጉ ጠቁመዋል።
የምክክር ሂደት ለማከናወን ፍላጎት እንዳለም ተነስቷል። ሆኖም ተከታታይ ውይይቶችን ማከናወን እንደሚጠይቅ እና የክልሉ ባለድርሻ አካላት ከፌደራል መንግስት ጋር ፖለቲካዊ ውይይት ማድረግ እንደሚሹ ነው የተነሳው።
ኮሚሽኑ ከዲያስፖራው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሃግብሩን ከሐምሌ 24 ጀምሮ በበይነ መረብ በአፍሪካ ከተለያዩ ሀገራት መከናወኑ ተመላክቷል።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ አጀንዳዎችን ለማሰባሰብ የሚረዳ መድረክ በነገው ዕለት እንደሚካሄድ ተንስቷል።
በቀጣይ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በሲውድንና በዱባይ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ለማካሄድ የቅድም ዝግጅት ስራዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ተነስቷል።
በ-ሰላም ይልማ












