የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ሁሉም የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የአብርሃምን ስምንነት” እንዲቀላቀል አሳሰቡ። የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ለእስራኤል ዕውቅና መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ሪፐብሊካኑ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል።
“በአሁኑ ሰዓት በኢራን ሲመረት የነበረው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።ሁሉም የቀጠናው አገራት አብርሃም ስምምነትን ቢቀላቀሉ ለእኔ አስፈላጊ ነው።” የሚል ጥሪ አቅርበዋል ትራምፕ።
በትራምፕ የመጀመሪያው ዙር የፕሬዚደንትነት ዘመን በአብርሃም ስምምነት ስም አረብ ኤሜሬቶች፣ ባህሬን ፣ሱዳንና ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጀመራቸው ይታወሳል።
እንደሳውዲ አረቢያ ያሉ አገራት ደግሞ ፍልስጤም የአገርነት እውቅና ሊሰጣት ይገባል በሚል ጉዳዩን በይደር ይዘውታል። ትራምፕ ቀጠናው ውጥረት ላይ ባለበት ሰዓት ይህን ማለታቸውም እያነጋገረ ነው ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ሙሉ ጋዛን እጠቀልላለሁ ባሉበት ቅጽበት ሪፐብሊካኑ የሰጡት አስተያየት ነው። በሌላ በኩል ሃማስ የእስራኤልን ፍላጎት ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ውድቅ አደርጎታል።
አልጀዚራ እንደዘገበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












