የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ ጋዛን ለመቆጣጠር የቀረበውን ዕቅድ ማጽደቁ ስጋት ፈጠረ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋዛን የመጠቅለል ውጥንና ጦርነቱን ለመቋጨት ይጠቅመኛል ያሏቸውን አምስት መርሆዎች ይፋ አድርገዋል ፡፡ ይህ ውሳኔ የጋዛውን ቀውስ ከትላንቱ ዛሬ የከፋ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የደህንነት ካቢኔው ለበርካታ ሰዓታት በእየሩሳሌም ከተሰበሰበ በኋላ የፀደቀ ዕቅድ ነው፡፡
አይ ዲ ኤፍ ጋዛን በቁጥጥሩ ስር እያዋለ ፤ከጦርነት ቀጠና ውጭ ባሉ አካባቢዎች ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ያደርጋልም ተብሏል፡፡ ምንም እንኳን ሰብዓዊ ድጋፍ ይደረጋል ቢባልም ውሳኔው የከፋ ውጤት ይኖረዋል የሚል ስጋት ጋርጧል፡፡
ጦርነቱን ለማቆም በሚል የተቀመጡ መርሆዎች ደግሞ ፡-
1.ሃማስን ትጥቅ ማስፈታት
2.በህይወት ያሉ ታጋቾችንና አስክሬን ማስመለስ
3.ጋዛን ትጥቅ ማስፈታት
4.የእስራኤል ጦር ጋዛን መቆጣጠር
5.የፍልስጤም አስተዳደርም ሆነ ሃማስ የሌለበት አማራጭ ሲቨሊያን መንግስት መመስረት ናቸው፡፡
ውሳኔው በሙሉ መንግስቱ መጽደቅ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












