የጀርመኑ ክለብ ፍራንክፈርት የክንፍ መስመር ተጫዋቹን ከፍራይበርግ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
በያዝነው የዝውውር አመስኮት ሁጎ ኤኪቲኬን ያጣው ፍራንክፈርት ጃፓናዊውን የክንፍ አጥቂ ተተኪ አድርጎታል። የቡንደስሊጋው ቡድን ለተጫዋቹ ዝውውር 20 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣እስከ 2030 የሚያቆየውን የ5 አመት ውል አስፈርሞታል።
የ27 አመቱ ዶዋን በተጠናቀቀው የውድድር አመት ፍራይበርግ የይሮፓ ሊግ ስፍራን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ካስቻሉ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ እንደነበር ይነገርለታል። በፍራይበርግ ቆይታው 123 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 26 ግብ ሲያስቆጥር፣23 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ለሃገሩ ጃፓንም 57 ጨዋታዎችን አድርጎ 10 ግብ በስሙ አስመዝግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












