የሊባኖስ መንግስት ሄዝቦላህን ትጥቅ ለማስፈታት ጦሩ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረበ፡፡
እስከ ታህሳስ ድረስ ሄዝቦላህ ትጥቅ ይፈታል የሚል ውጥን ቤይሩት አስቀምጣለች ፡፡ የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም ከአሜሪካ በኩል ግፊቱ በርትቶባቸዋል ፡፡ በኢራን የሚደፈገፈውን ሄዝቦላህን ትጥቅ ማስፈታት እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ በዋሽንግተን ተጠይቀዋል ፡፡
በሊባኖስ አንድ የመንግስት ጦር ብቻ መኖር እንደለበት መንግስት እምነቱ ሆኗል ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላም ከካቢኒያቸው ጋር ከስድስት ሰዓታት በላይ በጉዳዩ ላይ መክረዋል ፡፡
ጦሩ ይህ ወር እስከሚጠናቀቅ ድረስ እቅዱን አቅርቦ መንግስት እንዲወያይበት እና እንዲያጸድቀውም ጥሪ ቀርቧል ፡፡
ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












