የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያና ከዩክሬን መሪዎች ጋር ለመገናኘት ዝግጁ መሆናቸውን አሳወቁ።
የዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ወደ ሞስኮ በማቅናት ከፑቲን ጋር መወያየታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ለመወያየት ዝግጁነታቸውን መግለፃቸው ተሰምቷል።
ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የነበረው ውይይት መልካም እንደነበር ገልፀው፤ ከፑቲንም ሆነ ከዘለንስኪ ጋር ለመወያየት ዝግጁነታቸውን ተናግረዋል። ከሁለቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ጋር የሚያደርጉት ውይይት በመጪዎቹ ሳምንታት እንደሚሆን ይጠበቃል።
የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ አሜሪካ በሩሲያ ላይ እጥለዋለሁ ያለችው ማዕቀብ የሰአታት እድሜ በቀረው ጊዜያት ነው ወደ ሞስኮ አቅንተው ከፑቲን ጋር የተወያዩት፤ ትራምፕ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የተኩስ አቁም ካልደረሰች በሁሉም ከአሜሪካ ጋር የሚኖራት ንግድ ስርአት ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ማለታቸው ይታወሳል።
ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ ጋር ከፑቲን ጋር ከተወያዩ ኋላ ግን የደረሱበት ስምምነት ሆነ ከማዕቀቡ ጋር በተያያዘ የተባለ ነገር የለም። ከሩሲያም ሆነ ከአሜሪካ ባለስልጣናት በጥቅሉ ስብሰባው መልካም እንደነበር አንስተዋል።
ዘገባው የአር ቲ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












