የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡
የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጾ፣ በአደጋ ለሕልፈት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
መንግሥት ዜጎች በተለያዩ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ሚኒስቴሩ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሳስቧል፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












