በከተማዋ ቧንቧዎች ከደረቁ ሳምንታት መቆጠራቸው እየተነገረ ሲሆን ጉዳዩን ለማረጋጋት የቴህራን ባለስልጣናት የውሃ ፍጆታዎችን በመቀነስ ችግሩን ለማስቆም እየሰራን ነው ብለዋል።
የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሱድ ፔዚሽኪያን አስቸኳይ ውሳኔ ካልወሰንን ወደፊት መቋቋም የማንችለው ችግር ይገጥመናል በማለት ገልጸዋል። በኢራን 10 ሚሊዮን ሰዎች የውሃ እጥረት ውስጥ መሆናቸውን አንስተው ቀውሱ ከዚህ የባሰ እንዳይሆን የባለሙያዎች ፍራቻ ነው ሲሉ የቀድሞ የኢራን የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ሰይድ ማደን ተናግረዋል።
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ የእጥረቱ መንስኤ ደካማ የሆነ የውሃ አስተዳደር እና የህዝብ ቁጥር መጨመር እንዲሁም የአቅርቦት እጥረት ነው ተብሏል፡፡ ነገር ግን ቴህራን የገጠማት የውሃ እጥረት በዋናነት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰተ መሆኑ ነው የተነገረው።
በኢራን ውስጥ ከተከሰቱ ድርቆች መካከልም አስከፊ ሆኖም ተመዝግቦል። የሀገሪቱ የሙቀት መጠን በዚህ ወር 122 ድግሪ መድረሱም ተገልጿል። አየር ንብረት ባለሙያዎች ኢራን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሙቀት እንደሚገጥማት ተናግረዋል።
የቴህራን ባለስልጣናት ቀውሱን ለመቆጣጠር የውሃ አቅርቦት መጠንን በግማሽ መቀነሳቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም 80 በመቶ የሚሆን የቤተሰብ ክፍልን ጎድቷል ። በቴህራን በረጃጅም አፓርታማ የሚኖሩ ዜጎች የውሃ እጥረት አቅርቦት መቋረጡን አሳውቀዋል።
የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በከተማው በተሸከርካሪ ታንከሮች እየተከፋፈለ ሲሆን ነዋሪዎችም እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟቸው እንደማያውቅ እየተናገሩ ነው፡፡
ዘገባው የሲኤንኤን ነው
በ-አማኑኤል ምትኩ












