የሩሲያው ፕሬዚዳንት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ለሁለተኛ ጊዜ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ከሁለቱም ሀገራት መሪዎች ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሁለተኛ ጊዜ በስልክ መምከራቸውን ገልጧል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያው የስልክ ውይይታቸው በሶሪያና በኢራን ጉዳይ መምከራቸው ይታወቃል፡፡ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመካከላኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ ዙሪያ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውም ይታወሳል፡፡
ፑቲን በኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ጉዳይ የሚደረገውን ስምምነትም ቢሆን መደገፋቸው አልቀረም፡፡ ፑቲንና ኔታንያሁ የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ሲነገር ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯም እስራኤል በሩሲያ ላይ ማእቀብ ያለመጣሏ ይታወቃል፡፡
ዘገባው የኒውስማክስ ነው
በ-ትዕግስቱ በቀለ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












