የቀድሞው የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮ “የቁም እስር ” ተፈረደባቸው።
ቦልሶናሮ በፍርድ ቤት የተላለፈባቸውን ውሳኔ ችላ በማለት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ከቤታቸው እንዳይወጡ ታዘዋል። ፍርድ ቤቱ ምንም ዓይነት ማህበራዊ ሚዲያን የቀድሞው ፕሬዚዳንት እንዳይጠቀሙ ቢከለክልም እሳቸው ከውሳኔው ጋር የተቃረነ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ነው የተከሰሱት።
ቀኝ ዘመሙ ቦልሶናሮ በ2022 ምርጫ መሸነፋቸውን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል በሚል ቀደም ሲል መከሳሳቸው ይታወሳል። በልጃቸው እና በደጋፊዎቻቸው የሚጋሩ ንግግሮቻቸው የፍርድ ቤቱን ስራ የሚያጠለሽ እና የሚረብሽ በመሆኑ ማህበራዊ ሚዲያን ከመጠቀም ታግደውም ነበር።
የፕሬዚዳን ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫን መንግስት በሀይል ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል በሚል የተወነጀሉት ጄይር ቦልሶናሮ አሁን አዲስ ፍርድ ተቀብለዋል። በልጃቸው እና በቀድሞ የጦር ዓባል አማካኝነት በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ ጥሪ መቅረቡ ነው ለዚህ የዳረጋቸው።
ክልከላው ሶስተኛ ወገን ሳይቀር የ70 ዓመቱን ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛ ሀሳብ እንዳያጋራም ይደነግጋል። የአሁኑን ውሳኔው ተከትሎም የአሜሪካ መንግስት ብራዚልን ማውገዙን አሳውቋል።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












