ስዊድናዊው ተጫዋች በያዝነው የክረምት የዝውውር ገበያ ከኒውካስትል መልቀቅ እንደሚፈልግ መግልጹ እና ለብቻው ልምምድ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል።
ኒውካስትል ዩናይትድ አጥቂውን የመሸጥ ፍላጎት የሌለው ሲሆን፤ ሊቨርፑል ያቀረበለትን የ110 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ውድቅ አድርጎታል። የመርሲሳይዱ ክለብ በሌላ የተሻሻለ የዝውውር ሂሳብ ይመጣል ቢባልም ቀደም ብሎ ካቀረበው ሂሳብ መጨመር እንደማይፈልግ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
የ25 አመቱ ኢሳቅ ወደ ስፔን በመሄድ በቀድሞ ክለቡ ሪያል ሶሲዳድ ለብቻው ልምምድ ሲስራ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ወደ እንግሊዝ መመለሱ ታውቋል። ተጫዋቹ በግል ልምምዱን እየሰራ ዝውውሩን የመፈጸም እና ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎቱ ሳይሳካ ቀርቷል።
ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት በእስያ የሚገኘው ኒውካስትል በነገው ዕለት ወደ እንግሊዝ ሲመለስ አሌክሳንደር ኢሳቅም ዋናውን ቡድን ይቀላቀላል ተብሏል። ኢሳቅ አሁንም ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎት አለው የሚሉ መረጃዎች ግን አሁንም ተጠናክረው ቀጥለዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












