የስፔን ላሊጋው ክለብ ሶሲዳው ፖርቱጋላዊውን ተጫዋች ለመውሰድ ስለመስማማቱ ታማኝ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።
ወልቭስ በአውሮፓውያኑ 2022 ተጫዋቹን ከቫሌንሺያ በጊዜው የክለቡ ሪከርድ በሆነ 27.5 ሚሊዮን ፓውንድ ቢያስፈርመውም፤ አሁን ላይ በከፍተኛ መጠን ከስሮ 4 ሚሊዮን ፓውንድ ለመሸጥ ተስማምቷል።
ጉዌዴሽ ያሳለፍነውን የውድድር አመት የመጀመሪያ አጋማሽ በቤኔፊካ እና ሁለተኛውን አጋማሽ በቪላሪያል በውሰት ውል ማሳለፉ ይታወሳል። የ28 አመቱ ፖርቱጋላዊ በሶስት አመት የወልቭስ ያልተሳካ ቆይታው 33 ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድል ተሰጥቶት 5 ጎል ሲያስቆጥር፤ 3 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
የቀድሞ ክለቦቹ የስፔኑ ቫሌንሺያ እና የፖርቱጋሉ ቤኔፊካ ቢፈልጉትም የተጫዋቹ ፍላጎት የአንዳሉሲያውን ክለብ መቀላቀል ነው ተብሏል፡፡ ጉዌዴሽ በያዝነው የዝውውር ገበያ የሶሲየዳድ ሁለተኛው ፈራሚ ተጫዋች ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












