ዌስትሃም ዩናይትድ ለረጅም ጊዜ ላገለገለው የፊት መስመር ተጫዋች ሚኬል አንቶኒ የተሻሻለ ውል እንደማይሰጠው ታውቋል።
ሚኬል አንቶኒ በመዶሻዎቹ ቤት አሁን ያለው ውል የሚጠናቀቀው በያዝነው ወር መጨረሻ ሲሆን፣ውሉ ሲጠናቀቅ በነጻ ይለቃል ተብሏል።
የ35 አመቱ አጥቂ በታህሳስ ወር የመኪና አደጋ ካጋጠመው ወዲህ እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ከሜዳ ውጭ እንደነበር ይታወሳል። ከጉዳቱ ካገገመ በኋላ ለሃገሩ ጃማይካ የተወሰኑ ደቂቃዎችን መጫወት ችሏል።
ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ቡድናቸውን ይዘው አሜሪካ የሚገኙት አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር የተጫዋቹን ቆይታ በተመለከተ ብዙ አስተያየት የመስጠት ፍላጎት የለኝም ብለዋል።
ሚኬል አንቶኒዮ ዌስትሃምን የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 2015 ሲሆን፣268 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 68 ግቦችን በማስቆጠር የክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ መሆን ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












