የህክምና ማሽኖቹ ስራ ከጀመሩ 20 ወራትን ያስቆጠሩ ሲሆን ለአንድም ቀን አገልግሎት ሳይሰጡ የቀረቡት ቀን አልነበረም።
የጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን ያባሬ ሪፈራል ሆስፒታል በታህሳስ 2009 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያው እና ትልቁ የሶማሌ ክልል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው። ሆስፒታሉ ከጅጅጋ ከተማ ባሻገር፣ ከ7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች እና ከጎረቤት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ለሚመጡ ህሙማን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ሆስፒታሉ የአገልግሎት ጥራቱን እና ደረጃውን በማሳደግ የኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሆን አገልግት መስጠጥ የጀመረው ከጥር 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ጣቢያችን ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያም በክልሉን ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታልን ቅኝት አድርጓል። ሆስፒታሉ 2 የሲቲ ስካን እና 1 የኤም አር አይ ማሽን ባለቤት ነው። እነዚህ ማሽኖች ስራ ከጀመሩ 20 ወራትን አስቆጥረዋል አንድም ቀን ግን አገልግሎት አቋርጠው አያቁም ፤ እያንዳንዳቸው ማሽኖች በቀን ከ20 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳሉ።
የሲቲ ስካን እና የMRI ማሽኖች በመንግስት ሆስፒታሎች ሲሰሩ ማግኘት ብርቅ በሆነበት በዚህ ጊዜ በጅጅጋ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል 2 አመት ለሚጠጋ ጊዜ ያለ አንዳች መስተጓጎል አገልግሎት የሚሰጡ ማሽኖች የኖረበት አሰራር እና ልምድ ሁሉም ሊማርበት ይገባል።
የጅጅጋ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ከንጽህናው ጀምሮ ለህሙማን ህክምና ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነት ርህራሄን የሚያቀርብ ተቋ መሆኑን በስፍራው ተመልክተናል። የህክምና ባለሙያዎች መዳኒት አዛዝ ብቻ ሳይሆኑ ህሙማን የሚረዱ እና ሰብአዊነት የተላበሱ መሆናቸውን በተግባር የተመለከትንበት ተቋ ነው።
በቀን 700 እና በአመት ከ200 እስከ 300ሺ ታካሚዎችን የሚያስተናግደው ሆስፒታሉ ለተጨማሪ ህክምና የሚላኩ ታካዎችን ምጣኔን በእጅጉ መቀነስ መቻሉን የሆስፒታሉ የጥናት ዳይሬክተር ዶ/ር ኡስማን አሊ ተናግረዋል።
በመዲናችን አዲስ አበባ የሲቲስካን ፣ ኤም አራ ይ፣ የኩላሊት እጥበት እና መሰል አገልግሎቶችን የሚሰጡ የመንግስት ሆስፒታሎች ወደ ግል የህክምና ተቋት ሄዳቸው አሰሩ መባል የልማድ ያህል እየተዛመተ የሚገኝ ተግር ነው። በጅጅጋ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ግን በተቃራኒው የግል ተቋት እነዚህን አገልግሎችን ህሙማን በኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታሉ እንዲያሰሩ ያደርጋል።
በዚህም በቀን ከ30- 40 የሲቲስካን እና ከ20-25 የኤም አር አይ አግልግሎት የሚሹ ታካሚዎችን ሆስፒታሉ ያስተናግዳል።












