የድሩዝ ታጣቂዎች በሱዋይዳ አካባቢ በሚገኙ የሶሪያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከፍተው አንድ የመንግስት ወታደር ሲሞት ሌሎች መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡
በቅርቡ ተኩስ አቁም ላይ የደረሱት የድሩዝ ታጣቂዎች እና ሱዋይዳዎች እንደገና ወደ ጦርነት መመለሳቸው ለበርካታ ዓመታ በርስ በርስ ጦርነት ለፈራረሰችው ሶሪያ ሌላ ቁስል እንዳይሆንባት ከወዲሁ ተፈርቷል፡፡
በዱቡባዊ ሶሪያ ጥቃቱ መድረሱንም መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የሶሪያ ሰብአዊ መብት ተመልካች በአሁኑ ጥቃት አራት የሱዋይዳ ጎሳ አባላት ሲሞቱ ሌሎች ሶስት ታጣቂዎችም መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
ውጥረቱ በጊዜ የማይረግብ ከሆነ በጊዜያዊው የአህመድ አልሻራ መንግስት እና ሶሪያ ላይ ሌላ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ከወዲሁ ፖለቲከኞች እየተናገሩ ነው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው
በ-ቶማይ መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












