NBC Ethiopia
የእምነት ተቋማት ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት ስለ ሰላም የሚመከርበት 4ኛው የሰላም ኮንፍረነስ በሐረሪ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ሀይማናምኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ኮንፍረሱን አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። ኮንፍረነሱ በሀገሪቷ አንዳንድ አከባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም፤ ቅራኔዎችን በውይይት ለመፍታት ያለመ መሆኑን ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገልጸዋል።
ፍጹም ሰላምዊ ሀገርን ለመፍጠር ችግሮች ላይ በመምከር መፍትሄ የሚቀርብበት መድረኩ የተሳካ እንዲሆን የሀይማኖት ተቋማት፣ህብረተሰቡ እና የመንግስት አካላት ትብብር ያስፈልጋል ተብሏል። 4ኛው የሰላም ኮንፍረነስ በሐረሪ ክልል ሐረሪ ከተማ ሐምሌ 28 እና 29 ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃግብሩም ሰላምና አብሮነት ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች ላይ የሚመከርበት የፓናል ውይይት፣ህዝባዊ ውይይት የሚከናወንበት እንደሚሆን ተጠቁሟል። በመጨረሻም የሀይማኖት ተቋማት ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች ኃላፉነት የሚወስድበት ይሆናል ተብሏል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱት የሰላም ኮንፍረንሶች በርካታ ውጤቶች መገኘታቸው ተገልጿል። በተወሰነ መልኩ በአማራና ኦሮሚያ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ አካላት ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለሳቸውም እንደአብነት ተነስቷል።
በሰላም ይልማ












