የቻይና እና አሜሪካ የንግድ ተደራዳሪዎች ያለምንም መፍትሄ የሁለት ቀናቱን ውይይት አጠናቀቁ።
ሁለቱ አገራት በስቶክሆልም ሲደራደሩ ቢቆዩም ታሪፍ ከነሐሴ ጀመሮ አንዱ በሌላው ላይ የሚጥልበትን አሉታዊ አጋጣሚ ፈጥረዋል። እስካሁን ባለው የውጥረት ቀነ ገደብ መሰረት በነሐሴ 12 ታሪፉ በሁለቱም ሀይሎች በኩል የሚጀመር ይሆናል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሀላፊ ስኮት ቤሰንት የሁለት ቀናቱ ስብሰባ ገንቢ ነው ቢሉትም፣ እዚህ ግባ የሚባል ውጤት እንዳልተመዘገበበት ግን ኤን ቢ ሲ ኒውስ ጽፏል። ታሪፍ የመጣል ሂደቱን ለማራዘም ዕድሎች ሊኖሩ እንደሚችሉም የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ሳይቀሩ አሳውቀዋል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሀላፊ እና የንግድ ተወካይ ታሪፉን ስለመጣልም ሆነ ጊዜውን ስለማራዘም እስካሁን የተወሰነ ነገር እንደሌለ አረጋግጠዋል። ውሳኔው የዶናልድ ትራምፕ መሆኑን ያስታወሱት የአሜሪካ ተወካዮች ወደ ዋሽንግተን ተመልሰን ከሪፐብሊካኑ ትራምፕ ጋር እንመከራለን ብለዋል።
ጉዳዩ አሁንም ለውይይት ክፍት ሆኖ የሚዘልቅ ስለመሆኑም አጽንዖት ተሰቶበታል። ቤይጂንግ እና ዋሽንግተን የንግድ እንዲሁም የታሪፍ እሰጥ አገባ ውስጥ ከተዘፈቁ አምስት ዓመታት ነጉደዋል።
ዘገባው የ ሲ ኤን ኤን ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












