ለቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ሲንጋፖር የሚገኙት የማግፓይሶቹ አሰልጣኝ የፊት መስመር ተጫዋቻቸውን ቆይታ በተመለከተ አስተያየት ሰጥተዋል።
ትውልደ ኤርትራዊው አሌክሳንደር ኢሳቅ ከሳምንት በፊት ኒውካስትልን መልቀቅ እንደሚፈልግ መግለጹ ይታወሳል። አሰልጣኝ ሆው የተጫዋቹን ቆይታ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት “የኛ ዋነኛው ፍላጎት እሱን በክለባችን ማቆየት ነው፣መልቀቅ ከፈለገ ግን እኛ ልንወስንበት የምንችልበት መንገድ የለም “ ብለዋል።
ለተጫዋቹ ከሳዑዲ አረቢያ ክለቦች እና ከሊቨርፑል የዝውውር ጥያቄ ቀርቦላታል መባሉ ሃሰት ነው ያሉት አሰልጣኙ “ከየተኛውም ክለብ የዝውውር ጥያቄ እስከሁን አለመቅረቡን ገልጸዋል። አሰልጣኝ ኤዲ ሃው ይህንን ይበሉ እንጂ ተጫዋቹ ወደ መርሲሳይዱ ሊቨርፑል ለመጓዝ ፍላጎት ማሳየቱን እምነት የሚጣልባቸው መገናኛ ብዙሃን ዘግበውታል።
ሊቨርፑል በቀጣይ ጊዜያት ለተጫዋቹ ይፋዊ የዝውውር ሂሳብ ያቀርባል እየተባለ ሲሆን፣ኒውካስትልም ተተኪውን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። አሌክሳንደር ኢሳቅ ባሳለፍነው የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች 27 ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












