ህንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም ወሳኝ የተባለውን የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የህንድ ንግድ ሚኒስትር እና የእንግሊዝ የቢዝነስ የውጭ ጉዳዮች እና ንግድ ሚኒስትር ፈርመውታል። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተ ኬር ስታርመር እና የህንዱ ናሬንድራ ሞዲ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው ስምምነት ላይ የተደረሰው።
ታሪካዊ ነው የተባለለትን የነጻ ንግድ ስምምነት (FTA) አገራቱ መፈራረማቸው፣ የደልሂን እና ለንደንን ሁለንተናዊ ግንኙነት ያጠናክራል ። የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ወደ እንግሊዝ መጓዛቸውም የሚታወስ ነው።
ስምምነቱ ከሶስት ዓመታት ድርድር በኋላ በተሳካ መንገድ ተጠናቋል የሚል መረጃም ይፋ ተደርጓል። ዓመታዊ የንግድ ትብብራቸውን ወደ 25.5 ቢሊዮን ዩሮ ከፍ ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።
ሞዲ እና ስታርመር በሰሜን ምዕራብ ለንደን ወሳኝ ነጥቦችን አንስተው ተወያይተዋል። የህንድ እና እንግሊዝ የንግድ ስምምነት ለአሜሪካ የታሪፍ ዛቻ ምላሽ የሰጠም ነው።
ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












