ፈረንሳይ ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና ልትሰጥ መሆኑን አስታወቀች።
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ በመስከረሙ የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና እሰጣለሁ በሚል አረጋግጠዋል። “በአሁኑ ሰዓት አስቸኳዩ ጉዳይ ንጹሃንን ማዳን እና የጋዛውን ጦርነት ማስቆም ነው” ሲሉም ጽፈዋል ማክሮን።
በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ፈረንሳይ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና እንድትሰጥ ወስኛለሁም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ፈረንሳይ እውቅና ስትሰጥ አውሮፓ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገራት መካከል ግንባር ቀደም ያደርጋታል።
ኖርዌይ፣ አየርላንድ እና ስፔን ተመሳሳይ ሂደት ውስጥ እንደሚገቡም ምልክት ሰጥተዋል። ቢያንስ 142 አገራት ከ193 የመንግስታቱ ድርጅት ዓባላት ውስጥ ለፍልስጤም እውቅና ሰጥተዋል አሊያም እውቅና የመስጠት ሂደት ላይ ናቸው።
እስራኤል የማክሮንን ውሳኔ በጽኑ እንደምትቃወመውም ይፋ አድርጋለች።
ዘገባው የ ሲ ኤን ኤን ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












