የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 89/2017 ራሱን ችሎ እንዲዋቀር በአዲስ አበባ ም/ቤት መጽደቁ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ የኮሚሽኑ መቋቋምን እና በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ በጀት ዓመቱ ከ150 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ኮንፍረሶች መካሄዳቸው የተጠቆመ ሲሆን ይህ በኮንፍረንስ ቱሪዝም እየታየ ያለውን እድገት ለማጠናከርም ኮሚሽኑ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው የተገለጸው።
የኮሚሽኑ መቋቋም ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እንደሚግያዝ ያነሱት ኮሚሽነሩ ቱሪዝምን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል።
በ-ሰላም ይልማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












