በአፋር ክልል ሲከናወን የቆየው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደገ መምጣቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ።
የአፋር ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በዱብቲ ወረዳ ጉሩሙዳሌ ቀበሌ ዛሬ ችግኝ በመተከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።
በተለይም በማህበር የተደራጁ ወጣቶች በተሰጣቸው መሬት ፍራፍሬዎችና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን አልምተው ለውጤት በማብቃት ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን አንስተዋል።
የአፋር ክልል ለም መሬት በተለይም የአዋሽ ወንዝ በሚያልፋባቸው ወረዳዎች ለምርታማነት በሚያመቹ ቦታዎች እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ያሲን ዓሊ በበኩላቸው፤ በተለይም ክልሉ ሞቃታማ እንደመሆኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አስፈላጊነት የጎላ ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ተቋቁሞ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት ለመላቀቅ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡












