በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ 260 ሰዎች የሞቱበትን የህንድ አውሮፕላን አደጋ ተከትሎ የተሳሳቱ አስከሬኖች ወደ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እየተላኩ መሆኑን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሉም አስከሬኖች በሙያዊ ብቃት እና በክብር መያዛቸውን እንዲሁም ስጋቶችን ለመፍታት ከእንግሊዝ ባለስልጣናት ጋር እየሰራ መሆኑን ቢገልጽም፤ ይሁን እንጂ የተሳሳቱ አስከሬኖች ወደ ቤተሰቦች ግን እየተላኩ ይገኛል፡፡
አሾክ እና ሾብሃና ፓቴል ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ለመጎብኘት ወደ እነሱ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነበር ይህ አደጋ የደረሰባቸው፡፡ ልጃቸው ሚቴን ታዲያ እንደተናገረው ትክክለኛው የቤተስቡ አስከሬን እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡
አክሎም ይህን ስራ የሚሰሩት ሰዎች ብዙ ጫናዎች እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ትክክለኛውን አስከሬን ወደ ቤተሰብ የሚላክበት ስራዓት ሊኖር እንደሚገባ ግን አሳስቧል፡፡
ደይሊ ሜል የተሳሳቱ አስከሬኖች በእንግሊዝ ላሉ ዘመዶቻቸው ተመልሰዋል የተባሉባቸውን ሁለት ጉዳዮችን ዘግቧል። አንደኛው ቤተሰብ የተሳሳተ አስከሬን ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በአንድ የአስከሬን ሳጥን ውስጥ የበርካታ ሰዎች አስከሬን አካቷል፡፡
የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርቱን እንደሚያውቁት እንዲሁም ይህን ስህተት ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት በተደነገገው ፕሮቶኮሎች እና ቴክኒካዊ መስፈርቶች መሰረት ተጎጂዎችን የመለየት ስራም በድጋሜ እንደሚሰሩ አሳስበዋል ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ሔርሜላ ተመስገን












