በክልላችን ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የነበሩት ከሀጅ ጃሚኢ አደም አህመድ ከስራ ቦታ ወደ ጠላት መኮብለሉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ፔጅ በከሀጅ ጃሚኢ አደም እጅ የነበረ እና ፔጁም በግለሰቡ እጅ በነበረበት ሁኔታ ይዞ ኮብልሏል። ስለሆነም ግለሰቡ ከጠፋበት ቀን ጀምሮ ፔጁን ለመዝጋት ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን ስራዎች ሲሰሩ የቆዩና ፔጁ በወቅቱ የተዘጋ ቢሆንም፣ በዛሬው እለት 16/11/2017 ዓ.ም ግለሰቡ ፔጁን በመክፈት የራሱ የሆነ አላስፈላጊ መልዕክቶች ሊያሰራጭበት ችሏል፡፡
ይህም የሚያሳየው ግለሰቡ ፔጁን በማይታወቅ በግሉ አካውንትና ኢሜል እንደከፈተ እንዲሁም ለእኩይ ተግባር ከአራት ዓመታት በፊት መዘጋጀቱን ከጠያፍ ድርጊቱ ልንረዳ ችለናል፡፡
ስለሆነም አሁንም ፔጁ በከሀጅ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ በነበሩት በአሁኑ ሰዓት በወንጀል ተፈላጊ ከሀጅ ጃሚኢ አደም አህመድ እጅ የሚገኝ መሆኑን እንዲታወቅ ሆኖ፤ በአፋር ፖሊስ የፌስ ቡክ ፔጅ ላይ የሚለቀቁ ማንኛውም መልዕክቶች የክልላችን ፖሊስ ኮሚሽን የማይወክሉ መሆኑ ታውቆ ፔጁ ከፖሊስ ኮሚሽኑ ቁጥጥር ውጭ ስለሆነ እና ስለ ፔጁ ከሚመለከታቸው የቴክኒክ ባለሙያዎች ጋር ሆነን የመፍትሄ እርምጃ እስከምንወስድ በከሀጅ ጠላት እጅ በገባው ፔጅ በሚለቀቁ መልዕክቶች ህዝቡም ሆነ፣ የመንግስት አካላት እንዲሁም አባሎቻችን እንዳይደናገሩ ከወዲሁ የጥንቃቄ መልዕክት እያስተላለፍን፤ በቀጣይ ደኅንነቱ የተጠበቀ አዲስ ፔጅ በፖሊስ ኮሚሽናችን ስም ከፍተን የምናሳውቅ መሆኑን ጭምር እያሳወቅን ለተፈጠረው ችግር በተቋማችን ስም ይቅርታ እየጠየቅን አዲስ የምንከፍተው ፔጅ በክልላችን የመንግስት ኮሚኒኬሽን እና መንግስታዊ በሆኑ ሚዲያዎች የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
የአፋር ፖሊስ ኮሚሽን












