እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለችው በጅምላ የማስራብ ዘመቻ ከ100 በላይ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች አወገዙ።
ድርጅቶቹ መንግስታት አፉጣኝ እርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አቅርበዋል። ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ኦክስፉምና፣ ሜዲስንስ ሳን ፍሮንታየር የእስራኤል ድርጊት ካወገዙ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች መካከል ይገኙበታል።
እስራኤል በጋዛ ያሉ የሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይገቡ በማገድ፣ በመቆጣጠርና ፣ እርዳታ የሚከፉፈልባቸው ስፍራዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ፍልስጤማውያን ለከፉ ረሀብና ሞት እንዲዳረጉ ሆነዋል።
ህፃናት በምግብ እጥረት መቀንጨር ሲዳረጉ፣ በእድሜ ከፍ ያሉት ደግሞ በረሀብ በየመንገዱ ሞተው ማገኘት እየተለመደ መጥቷል። እንደ ጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ መሰረት ባለፉት 24 ሰዓታት እንኳ ከ10 በላይ ፍልስጤማውያን በረሀብ ሞተዋል።
እስራኤል ካለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት አንስቶ ምንም አይነት የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በመከልከል በርካታ ጥፋቶች እየደረሱ ይገኛሉ ተብሏል። የተባበሩት መንግስታት ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ፤ አሁን ደግሞ 109 ዓለምአቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ድርጊቱን ከማውገዝ ባሻገር ጫና ለመፍጠር እየሰሩ ነው ሲል ቢቢሲ እና አልጀዚራ ዘግበውታል።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












