የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4 ኪሎ ህፃናት እና ወጣቶች ቲያትር (ወክማ) አካባቢ ለ4ተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እንደገለጹት መንግስት ባለፉት 3 ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ማኖር የሚል መርሀ-ግብር ቀርጾ ከ40 ቢሊየን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን አስታውሰዋል፡፡
አሁንም ችግኞችን እንተክላለን፣ ልማታችንን እናስቀጥላለን፣ ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን ሲሉም ገልፀዋል፡፡ አክለውም የሰው ልጆች የተፈጥሮ ሚዛንን ጠብቀው ባለመኖራቸው በተለይም እንደ አፍሪካ ያሉ ዝናብን መሰረት አድርገው እርሻ የሚያርሱ አገራትን ላይ የተለያዩ ችግሮችን ያስከተለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ስራ እነሆ ተጀምሯል ያሉት ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ነገ የልጆቻችን ጥላ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በቀጣም የችግኝ ተከላ መርሀግብሩ እንደ አገር ቀጣይነት ያለው አስተማማኝ ኢኮኖሚ፣ ልማት እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ ዘንድሮ የተያዘውን አገራዊ እቅድ ለማሳካት እንስራ ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የምክር ቤት አባላት፣ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊዎችና አመራሮች፣ ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሬ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
መረጃው የምክር ቤቱ ማህበራዊ ትስስር ነው












