በደካማ ይለፍ ቃል ሳብያ በመረጃ መንታፊዎች ውድመት እንደደረሰበት የተነገረው የ158 ዓመት ድርጅቱ፣ በዚህ ምክንያት 700 ሰዎች ስራቸውን ለማጣት ተገደዋል ተብሏል።
የሰሜን ትራንስፖርት ድርጅት ብሪታንያ ውስጥ ከሚገኙ በተደጋጋሚም በመረጃ መንታፊዎች አደጋ ከሚደርስባቸው ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው። በብሪታንያ ትልልቅ ስም ያላቸው እንደነ M&s co_op እና Harrods የንግድ ድርጅቶች በቅርብ ወራት ውስጥ ተመሳሳይ የሳይበር ምዝበራ በመረጃ ምንተፍዎች አጋጥሟቸዋል።
የco-op ሀላፊ ባለፈው ሳምንት እንደገለፁት 6.5 ሚሊዮን የሰራተኞች መረጃ መሰረቁን ተናግረዋል። እንደ KNP ገለፃ መረጃ መንታፊዎች ወደ ኮምፒውተር ሲሰተም በመግባት የሰራተኞችን የይለፍ ቃል በመገመት የድርጅቱን መረጃ በመስረቅ ሲስተሞችን እንደቆለፉባቸው አሳውቀዋል።
በ2023 በተመሳሳይ በመረጃ መንታፊዎች አደጋ የደረሰበት ድርጅቱ፣ የተሰረቁ መረጃዎችን ማስመለስ የሚቻለው ብቸኛ መንገድ በዚህ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ዋጋ እንዲከፍሉ በማድረግ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
እንደ KNP ዳይሬክተር ፓውል ማብራሪያ ከሆነ፣ መረጃ መንታፊዎች የሰረቁትን መረጃ ለማስመለስ 5 ሚሊዮን ፓወንድ መጠየቃቸውን ገልፀው፤ ነገርግን ድርጅታቸው ያን ያህል ገንዘብ የለውም በማለት መረጃዎቹ መጥፋታቸውንና ድርጅቱም መክሰሩን አረጋግጠዋል።
የብሪታንያ ብሔራዊ ሳይበር ደህንነት ማዕከል በበኩሉ፤ ብሪታንያን ደህንነቷ የተረጋገጠ መኖሪያ የማድረጉ ጉዳይና አስተማማኝ የበይነ መረብ ንግድ እንዲኖር ይሰራል ብለዋል። የሳይበር መዝባሪዎች ምንም የተለየ አዲስ ነገር አይሰሩም ያሉት ሀላፊው ደካማ የሚስጥር ኮድ ያላቸውን ብቻ እየፈለጉ እንደሚያጠቁ ነው የገለፁት።
ማዕከሉ እንዳስታወቀው መንታፊዎች መረጃ ከሰረቁ በኋላ ማስመለሻ ገንዘብ እንደሚጠይቁ በመናገር፣ በባለፈው ዓመት ብቻ 19, 000 የመረጃ ስርቆት በብሪታንያ የንግድ ድርጅቶች ላይ ተፈጽሟል ብለዋል።
ባለፉት ጥቅት ዓመታት ውስጥ በርካታ የሳይበር ወንጀሎችን እያየን ስለሆነ ድርጅቶች የመረጃ ቋት ደህንነታቸውን በጠንካራ ኮድ ልጠብቁ ይገባልም ነው ያሉት። የKNP ሀላፊ ድርጅቶች ጠንካራ የቴክኖሎጂ ጥበቃ በማድረግ ከሳይበር መዝባሪዎች መረጃዎቻቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።
በ አማኑኤል ምትኩ












