የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦር ካዘመተች ከሶስት ዓመታት በኋላ ግዙፍ የተባለውን ሹም ሽር አድርገዋል፡፡ የ39 ዓመቷ ዩሊያ ስቪሪዴንኮ ከዴኒስ ሽምይሃል ስልጣኑን ተረክበው ተተክተዋል፡፡
ስቭይሪዴንኮ ቀደም ሲል ተቀዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በተጨማሪም የኢኮኖሚ እድገትት አሊያም ልማት እና ንግድ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር ዲፕሎማሲያዊ ስራ ለመስራት በሩ ተከፍቶላቸዋል፡፡
በብርቅዬ ማዕድናት ድርድር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ኪዬቭን እና ዋሽንግተንን በመግባባቱ ረገድም ብዙ ሚና ነበራቸው ተብሎላቸዋል፡፡ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር በሶሻል ሚዲያቸው ላይ ባጋሩት መልዕክትም የዩክሬንን የአገር ውስጥ የጦር መሳሪያ ምርት አቅም እንደሚያሳድጉ እና ጦሩን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ነረጋግጠዋል፡፡
ዩክሬን በራሷ መንገድ እንድትቆም እሰራለሁ ያሉት አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ማህበራዊን እና ኢኮኖሚያዊ መሰረቶች ላይም ትኩረት ይደረጋል ብለዋል። በጦርነት ውስጥ ላለችው ዩክሬን አፋጣኝ ስራዎችን በመስራት ህዝቡን ነገ ዛሬ ሳልል ከቀውስ ለማውጣትም እሰራለሁ በሚል ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












