በሊቢያ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ከአንድ መቶ በላይ ስደተኞች መለቀቃቸው ተሰምቷል
አምስት ሴቶችን ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ ስደተኞች በምስራቅ የሊቢያ ግዛት በህገወጦች ተይዘው ሲሰቃዩ የነበሩ ነጻ መውጣታቸውን የሊቢያ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከሊቢያ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በወንጀለኞች ቡድን ተይዘው ነጻነታቸውን አጥተው በግዳጅ ሲዘዋወሩ የነበሩትን ስደተኞች ለማስለቀቅ ህገወጦቹ አዘዋዋሪዎች ከቤተሰቦቻቸው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ይጠይቁ እንደነበረም ነው ያስታወቀው።
ዘገባው የኤዢያ ዋን ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












