በደቡባዊ ሶሪያ ሱዋይዳ ግዛት በታጠቁ የቤዱይን ጎሳ ተዋጊዎች እና በድሩዜ ሚሊሻዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል።
የሶሪያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አናስ ኻታብ እንደገለጹት፣ በሱዋይዳ አል-ማኩስ ሰፈር በአካባቢው በታጠቁ ቡድኖች እና በአካባቢው ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይውት እንደጠፋ ገልጸው ከፍተኛ ስጋት በአካባቢው እንዳለ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩም በደቡባዊ የሱዋይዳ ግዛት እና ገጠራማ አካባቢዎች ለተከሰተው ውዝግብ ዋነኛው ምክንያት የመንግስት ተቋማት በተለይም ወታደራዊ እና የፀጥታ አካላት አለመኖራቸው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አክለውም የሀገሪቱ መከላከያ ጦር በግዛቱ ውስጥ በመግባት ግጭቱንን ለማስቆም እንዲሁም የጸጥታ ጥበቃ ለማድረግ እና ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የደህንነትን እርምጃዎችን እና የተቋማትን ሚና በመገንዘብ የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሁም የህዝብን ህይወት ወደ መደበኛ ሁኔታው እንዲመለስ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል ኻታብ፡፡
የሀገሪቱ የዜና ወኪል እንደዘገበውም በርካታ የሰራዊት ሃይሎች ጸጥታን ለማስጠበቅ ሲሞክሩ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል፡፡
አናዶሉ እንደዘገበው
በ ሔርሜላ ተመስገን












