የቀድሞው የሊቨርፑል አወዛጋቢ አጥቂ ኤል ሃጂ ዲዩፍ ሞክሼ ወደ ለንደኑ ክለብ ለመዘዋወር በግል ጉዳዮች አስቀድሞ ስምምነት መፈጸሙን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ዌስትሃም ለሴኔጋላዊው ተካላካይ 20 ሚሊዮን ፓውንድ የሚከፍል ሲሆን፣ተጫዋቹ የህክምና ምርመራውን በያዝነው ሳምንት ያጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። መዶሾቹ በዝውውር ገበያው ዲዩፍ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው በመሆን የአሰልጣኝ ግራሃም ፖተርን የቡድን ስብስብ ይቀላቀላል።
የ20 አመቱ ኤልሃጂ ማሊክ ዲዩፍ በዘንድሮው አመት ሻምፒዮን በሆነው ስላቪያ ፕራግ 27 ጨዋታዎች ላይ በቋሚ ተሰላፊነት መጫወት ችሏል።ዌስትሃም በቅርቡ የሸጠውን ወሳኝ የፊት መስመር ተጫዋቹን ሞሃመድ ኩዱስን ምትክ ይገዛል ተብሎም ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












