ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኩላሊት ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጡ 20 የዲያሊሲስ ማሽን እና 10 ዘመናዊ አልጋዎችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከቧል።
ድጋፉ ለ180 ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ለ3 ዓመታት የሚሆን የዳያሊስስ ግብዓቶች ከወንበሮች ጋር ይዟል ነው የተባለው።
ሜድሮክ ያደረገው ድጋፍ፣ ከአምስት ዓመታት በፊት በምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ እና ዘዉዲቱ ሆስፒታሎች የተቋቋመውና በየዓመቱ እስከ 25 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አቅም ላነሳቸው 144 ታማሚዎች በየሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ያጠናክራል ተብሏል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት “የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በህሙማን፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እናመሰግናለሁ” ማለታቸውን ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












