ሶሪያ እና ግዙፉ የአረብ ኤሚሮአቶች ዲፒ ዎርልድ ኩባንያ የስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ‘የወደብ ስምምነት’ ላይ ደረሱ፡፡ የዲፒ ዎርልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶሪያ እጅግ ዋጋ ያላቸውን ሀብቶች በእጇ አስገብታ ትንቀሳቀሳለችም ብለዋል፡፡
አዲሱ የሶሪያ መንግስት በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መቀመጫውን ካደረገው ግዙፍ ድርጅት ጋር “የታርቱስ ወደብ ልማት” ስምምነት ላይ ሲደርስ ግንባር ቀደም ዓላማው የአገሪቱን ድህረ-ጦርነት ኢኮኖሚ ዳግም ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ጭምር ነው ተብሏል፡፡
ስምምነቱ ደማስቆ ውስጥ በዲፒ ዎርልድ እንዲሁም በምድር እና ባህር ጠቅላላ ባለስልጣን መካከል ተፈርሟል፡፡ በሥነ -ሥርዓቱ ላይ ጊዚያዊ ፕሬዚዳንቱ አህመድ አል-ሻራዓ’ መገኘተቻውም ተነግሯል።
የሶሪያ ባለስልጣናትም ስምምነቱን የአገሪቱን የሎጂስቲክ መሰረተ ልማት ለማዘመን ቁልፍ ዕርምጃ ነው ብለውታል፡፡ የአሳድ መንግስት ከተገረሰሰ ወዲህ የአል-ጁላኒ መንግስት ዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ለመግባት ወሳኝ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረቱንም አድርጓል።
ከፊርማ ሥነ -ሥርዓቱ በኋላ የዲፒ ዎርክድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሱልጣን አህመድ ቢን ሱላየም እንዳሉት “የታርቱስ ወደብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በማንሰራራቱ ረገድ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታል፡፡”
ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












