በእስራኤል ጥቃት በጋዛ የሕክምና ተቋም ላይ ጉዳት በመድረሱ የአስር ሕጻናት ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡
ሕክምና በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ ከተገደሉት 16 ፍልስጤማውያን መካከል በትንሹ 10 የሚሆኑት ህፃናት መሆናቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ ተኩስ አቁሙ ሁኔታ በድርድር ላይ ሳለ በዴር አል ባላህ ሃሙስ ዕለት በገሃድ ጥቃት መፈጸሙ የተራድኦ ቡድኖቹ ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ህግጋትን የጣሰ ነው ሲሉ ጠርተውታል።
ሮይተርስ አረጋግጫለው ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አቧራ እና ጩኸት ብሎም በርካታ ሰዎች ተጎድተው የሚያሳይ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ የእስራኤል ጦር በሀማስ መሪነት በጥቅምት 7 በተካሄደው ጥቃት የተሳተፈ ታጣቂን መምታቱን ገልፆ ተጎጂዎችን በተመለከተ ዘገባዎችን ተመልክተናል እና ክስተቱ በምርመራ ላይ ነው ሲል አስታውቋል፡፡
ዘገባው የዘ ኢንዲፔንደት ነው፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












