በእንግሊዝ የሚገኝ አንድ ዩንቨርስቲ ያወጣው ጥናት እንደሚያሳየው ጭንቀት ያለባቸው ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የበለጠ የተጠቁ ናቸው ሲል አስነብቧል።
የታዳጊዎች የአእምሮ ጤንነት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደገባ የተገለጸ ሲሆን ይህ በታዳጊ ዕድሜ ላይ ባሉ ወጣቶች መካከል የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር እንደሚገናኝ ጥናቱ አመላክቷል።
በጥናቱም በእንግሊዝ ውስጥ ማህበራዊ ሚዲያ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎች ከ7-19 አመት እድሜ ክልል ውስጥ ካሉት ስድስት ህጻናት መካከል አንዱ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሎል።
እነዚህ ታዳጊ ወጣቶች የአእምሮ ሕሙማንን ግማሽ ያህሉን ሊወክሉ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ይህም የወደፊት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምርታማነትን ይጎዳል። ስልክን አዘውትሮ መጠቀም ከአእምሮ ጤና ማጣት ጋር በተለይም ከድብርት ጋር የተያያዘ ነው።
ማህበራዊ ሚዲያ በአእምሮ ጤነኛ ከሆኑ ሰዎች ይልቅ የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተገልጾል። በ 3,340 ወጣቶች ላይ በተካሄደው ጥናት፤ 16% የሚሆኑት ከ11-19 አመት እድሜ ያላቸው ታዳጊዎች አንድ ወይም ከዚያ በላይ የአዕምሮ ጤና ችግር አለባቸው፡፡
በዚህም ከጤናማ ታዳጊዎች ጋር ሲነፃፀሩ የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ እንዲሁም በማህበራዊ ህይወታቸው ደካማ ናቸው።
ጥናቱ በማጠቃለያውም የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ታዳጊ ወጣቶች የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችውን ማስተካከል እንዳለባቸው እና በስሜታቸው ላይ ያለውን ተፅእኖ እንዲቆጣጠሩ ምክረ ሀሳቡን አስፍሮል።
በ ሔርሜላ ተመስገን












