የዩክሬን መዲና ኬቭ ለሊቱን መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ስትደበደብ እንዳመሸች ተገለፀ።
የዩክሬን የሀገርውስጥ መገናኛ ብዙሀን ባጋሩት መረጃ መሰረት የከተማዋ በርካታ አካባቢዎች መደብደባቸውንና እስካሁን ስምንት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል። በጥቃቱ የመኖሪያ ቤት ህንፃዎች ፣ ተሽገርካሪዎች፣ የገበያ ማዕከላት እና ሌሎችም በርካታ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን የኬቭ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የዩክሬን ወታደሮች እንዲሁ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚሳኤል ጥቃት እንዳይሰነዘር ስጋታቸውንና የድሮን ጥቃቱን ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። ሩሲያ ትላንት አመሻሽ ከዚህ ቀደሙ የከፉ ነው የተባለለትን መጠነሰፊ የድሮን ጥቃት ማድረሷ ተገልጿል።
ከለሊት አስከ ማለዳ የነበረውን የኬቭ ድብደባ ተከትሎ እስካሁን ከሞስኮ የተባለ ነገር የለም።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












