። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
ለብሪክስ ጉባኤ ብራዚል- ሪዮ ዴጄኒየሮ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይና አቻቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ በማህበራዊ ገጻቸወሰ ባሰፈሩት መልእክት:-
“ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል።” ሲሉ አስታውሰዋል።
ከቻነፈይና ጋር ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር በማከልትም ሲጠቅሱ፣ “ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል።” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ።












