የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በወቅታዊና ኮሚሽኑ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን አስመልክቶ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ እየሰጡ ባሉት መግለጫ በትግራይ ክልል ምክክር ለማካሄድ የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ኮሚሽኑ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ደብዳቤ ፅፎ ምላሽ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምላሽ እስኪመጣ ድረስ በክልሉ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው ነባራዊ ሁኔታ የምክክር መድረክ ለማስጀመር የሚያስችል አለመሆኑን በመግለፅ ይህም በኮሚሽኑ ስራ ላይ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ነው ቃል አቀባዩ ያብራሩት።
በምክክር ሂደቱ ላይ ተሳታፊ ሆነው በመሀል አቋርጠው የወጡ 4 የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሂደቱን ባቋረጡበት ምክንያት ዙሪያ ለመወያየት መድረክ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።
እስካሁን ያልተሳተፉ በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለማሳተፍ የተለያዩ ጥሪዎችን ኮሚሽኑ ለቡድኖቹ ቢያደርግም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቀዋል።
በ – አክረም ኑርያ












