፡፡ ። ። ። ። ። ። ። ። ።
የየመን ሁቲዎች እስራኤል ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፡፡
ጥቃቱ የቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያን በዋናነት ዒላማ ያደረገ ሲሆን፣ ከባድ መልዕክት ለእስራኤል ያስተላለፈ ሆኗል፡፡
የሁቲው ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ ሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳዔል ጥቃም ላይ መዋሉንም ይፋ አድርገዋል፡፡
ሌሎች ሶስት አካባቢዎችም በሰው አልባ አውሮፓላኖች (ድሮንስ) መመታታቸውን ያህያ ሳሬ አሳውቀዋል፡
ጥቃቱ ዓላማውን አሳክቶ ሚሊዮኖች ወደ መጠለያ እንዲገቡ አድርጓል ያሉ ሲሆን፣ የቤን ጉሪዪን አየር መንገድም ስራ እንዲያቆም አድርገናል በሚል ሀሳባቸውን ሰተዋል፡፡
በሌላ በኩል የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሚሳዔሉን መወንጨፍ ተከትሎ አጸፋው ይከፋል በሚል ዝተዋል።
ካትዝ የሰንዓን አስተዳደር ከቴህራን ጋር ለማመሳሰል ሞክረዋል።
በእስራኤል ላይ እጁን ያነሳ ሁሉ “እጁን ይቆረጣል” በሚልም አስጠንቅቀዋል እስራኤል ካትዝ፡፡
ይህ ውጥረት መካከለኛ ምስራቅን ወደ ባሰ አደጋ ይከተዋል የሚል ስጋትም ተደቅኗል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












