የተነፈግነው ፍትህ ካልተመለሰ ጉዳዩን ወደ ፊፋ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ወስደዋለሁ ብሏል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሰጠው ተገቢነት የሌለው ውሳኔ እጅግ አሳዝኖናል ያለው ክለቡ ተጫውተን አሸንፈናል ሲል መግለጫውን ይጀምራል።
የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የታገዱ ተጫዋቾችን አሰልፎ ከሆነ በጥሎ ማለፉ ያሸነፋቸው ክለቦች በሙሉ ፎርፌ አግኝተው ጉዳያቸው እንደገና መታየት አለበት እንደ ማለትም ይሆናል ያለ ሲሆን እርስ በርስ የሚጣረስ ሀሳቦችን በማገናኘት ውጤቱን ለመቀማት መሞከር ተገቢና ህግን የተከተለ ውሳኔ አይደለም ብሏል።
ፌዴሬሽኑም ዉሳኔውን ከህግጋቱ ጋር በማገናዘብ እንደገና እንዲያጠነዉ ቅሬታችንን እናሰማለን ያለው ክለቡ ደጋፊዎቹና የስፖርቱ ቤተሰብ ከጎናችን መሆኑን እንገልፃለን ሲል ገልጿል።
ፌደሬሽኑ ውሳኔውን በተገቢው መልኩ እንዲያጤነው በአክብሮት እየጠየቅን፣ የተነፈግነው ፍትህ እስኪመለስ ጉዳዩን እስከ ፊፋ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት ድረስ በይግባኝ ወስደን ለጉዳዩ ተገቢው እልባት እስኪሰጥ ድረስ የክለቡ ቦርድ ቁርጠኛ መሆኑን እንገልጻለን ብሏል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትላንት ባስተላለፈው መግለጫ ዙሪያ ዛሬ ከሰዓት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












