በዓለም የክለቦች ዋንጫ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሪያል ማድሪድን ከ ጁቬንቱስ ያገናኘው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በማድሪድ 1-0 ድል አድራጊነት ተጠናቋል።
ሎስ ብላንኮዎቹ በኳስ ቁጥጥር ፍጹም ብልጫ በወሰዱበት ጨዋታ ብቸኛዋን ግብ ወጣቱ አጥቂ ጎንዛሎ ጋርሺያ አስቆጥሯል። የዣቪ አሎንሶ ቡድን በጨዋታው ያሳየው እንቅስቃሴ እስካሁን በመድረኩ ከነበረው እጅግ የተሻለ ሆኖ ታይቷል።
ማድሪድ በዩቬ የግብ ክልል በተደጋጋሚ መድረስ የቻለ ሲሆን 11 ፍጹም ያለቀላቸው የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል። በተመሳሳይ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ንጋት ላይ ቦሩሲያ ዶርትሞንድ ሞንቴሪን 2-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።
የዶርትሞንድን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ሴህሩ ጉራሲ ሲያስቆጥር፣ ሞንቴሪን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ቤርትራሚ ከመረብ አገናኝቷል። የሜክሲኮው ክለብ ሞንቴሪ በጨዋታው በኳስ ቁጥጥር እና ኢላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎች በማድረግ የተሻለ መሆን ቢችልም ከሽንፈት አላመለጠም።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












