በጉሮሮዋ ላይ የተጣበቀውን የዓሣ አጥንት በአጋጣሚ የዋጠችው ታይላንድዊ ሴት ማውጣት ሳትችል በመቅረቶ ህይወቷ ላይ አደጋን ጥሏል።
ሳንግ ላን ለሚዲያዎች እንደገለጸችው የአሳ ሾርባ እየተመገበች በነበረበት ወቅት በአጋጣሚ የዓሳ አጥንት የዋጠች ሲሆን አንገቷ ላይም ከባድ ህመም እንደተሰማት አብራርታለች።.ባህላዊ መድሃኒቶችን በመጠቀም አጥንቱን ለመንቀል ሙከራ እንዳደረገች ብትገልጽም ነገር ግን ምንም ዓይነት መፍትሄ እንዳልሰጣት ተናግራለች።
ወደ ሆስፒታል የሄደችው ሳንግ በኤክስሬይ ምርመራ ምንም ዓይነት ምልክት ግን ሊታይባት አልቻለም ነበር። ምንም እንኳን የኤክስሬይ ምርመራውን ተከትሎ በጉሮሮዋ ላይ በተሰማት ህመም አጥንቱ እንደተነቀለ አስባ ነበር።
ሳንግ ላን በጉሮሮዋ ላይ ያለውን ምቾት ማጣት ተላምዳ እየኖረች የነበረ ቢሆንም፤ ግን ከሁለት ሳምንታት በኋላ አንገቷ እንዳበጠ አስተዋለች። ይህን ሁኔታ ግን ከታይሮይድ ዕጢ ጋር የተገናኘ እንደሚሆን በመጠርጠር በድጋሚ ወደ ሆስፒታል አቀናች፡፡
በሁለተኛውም ህክምና አንገቷን በድጋሜ የኤክስሬይ ምርመራ ቢደረግም ምንም አዲስ ነገር አልተስተዋለም ነበር፡፡ የህክምና ባለሞያዉም አንዳንድ መድሃኒቶችን እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በመስጠት ወደ ቤቶ እድትመለስ አድርጎል፡፡
ሳንግ ላን የህመም ማስታገሻዎቾን በመውሰድ ላይ በነበረችበት ወቅት አንገቷ አካባቢ አንድ ሹል መርፌ የሚመስል ነገር ሲጫናት አስተዋለች። በሁኔታው የተደናገጠችው ሳንግ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ተመለሰች እናም በመጨረሻም ዶክተሮቹ 2 ሴንቲ ሜትር የሆነ የዓሣ አጥንት ከ ሳንግ ላን አንገት ላይ ማውጣት ችለዋል።
በሳንግ ላን ላይ ቀዶ ጥገና ያደረገው የህክምና ቡድን ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ነገር አይቶ እንደማያውቅ ገልጿል። ሳንግ ላን ከቀዶ ጥገናው በሆላ እንደተናገረችው ለተወሰነ ጊዜ ምናልባትም በቀሪው ህይወቷ ምንም ዓይነት የዓሳ ምርት እንደማትጠቀም ገልጻለች፡፡ አሳን መብላት ለሚወዱ ሰዎችም ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች፡፡
በ ሔርሜላ ተመስገን












