የኢትዮጵያ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ መረጃን መሰረት ያደረጉ የጤና ችግሮችን በመለየትና ፈጣን ሪፖርት በማድረግ በሽታን ለመከላከል የሚያግዝ ነው።
በኮንፈረንሱ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በህብረተሰቡ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን በመረጃ ቀድሞ በመለየት ፈጣንና ቀልጣፋ ሪፖርት በመጠቀም የህክምና አገልግሎትን ለመስጠት ብሎም በሽታን ለመከላከል የሚያግዝ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስልጠናው እንዲሰጥ በማድረግ በሽታን ቀድሞ ከመከላከል አንስቶ ፈጣን ህክምና ለመስጠት የሚረዳ መሆን ነው የገለጹት።
ሚኒስትሯ ተለዋዋጭ በመሆነው ዓለም ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታ ስርጭት ስጋት በመኖሩ ፤በስልጠና የዳበሩ ባለሙያዎችን በማፍራት የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮግራም መሆኑን ጠቁመዋል።
ስልጠና ከመስጠት ባሻገር በፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግን አልሞ መስራት እንደሚገባ ነው የጤና ሚኒስትር ዶክትፕር መቅደስ ዳባ ያሳሰቡት።
የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፓትሪክ ኦኩማ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ የስልጠና ፕሮግራም ውጤታማ ከሆኑ ፕሮግራሞች አንዱ መሆኑን በመግለጽ ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ በመስራት ብቁ ባለሙያዎችን ከመፍጠር አኳያ አበረታች ስራ መስራቷን ጠቁመዋል።
ጉባኤው ለ3 ቅናት የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ ውይይቶች እንዲሁም የልምድ ልውውጥ የሚካሄዱበት እንደሆነ ይጠበቃል።
በ-ሰላም ይልማ












