ቤዥክታሽ የ27 ዓመቱን አጥቂ ዝውውር በፍጥነት ለመቋጨት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
ታሚ አብራሃም”ሄሎ ጥቁር ንስሮች ወደ እናንተ እየመጣሁ ነው አየር መንገድ እንገናኝ” የሚል ልጥፍ በማህበራዊ የትስስር ገጹ በኩል አጋርቷል። ተጫዋቹ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሚላን ቤት ያሳለፈ ሲሆን በሴሪ ኤው 8ኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው ክለቡ 10 ጎሎችን አስቆጥሯል።
ሆኖም ግን ሚላን የውሰት ዉሉን ወደ ቋሚነት ለመቀየር አልፈለገም። የእግር ኳስ ህይወቱን በቼልሲ የጀመረው ታሚ አብራሃም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በ11 ጨዋታዎች ተሰልፎ 3 ጎሎችን አስቆጥሯል።
በ2021 በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ሮማን ከመቀላቀሉ በፊት ለብሪስቶል ሲቲ፡ ስዋንሴና አስቶን ቪላ ክለቦች በውሰት ዉል ተጫውቷል። የመዲናው ክለብ በአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ስር የ2022 የኢሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ የእንግሊዛዊው አጥቂ አበርክቶት ጉልህ ነበር።
በ-ይበልጣል ሰውነት
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












